restoring our biblical and constitutional foundations

                

አንድ ‹‹ዋና መጋቢ›› ብቻ አለ እርሱም እኛ አይደለንም

 David Alan Black  

ምናልባት ማንም ‹‹ዋና መጋቢ›› የሚል መጠሪያ ሊኖረው ይችላል፡፡ እርግጠኛው ግን ሐዋሪያው ጴጥሮስ ነው፡፡ ከወንጌል የምንማረው በደቀ መዛሙርት ማካከል የተለየ ሥፍራ ተሰጥቶታል፡፡ ከዘቤዴዎስ ልጆች ጋርና ከወንድሙ ከእንድሪያስ ጋር ለጌታ የተሰበሰቡትን የቅርብ ሰዎች ይወክላል፡፡ እንደ ማር 1፡16 ኢየሱስ በመጀመሪያ ከጠራቸው ደቀመዛሙርት አንዱ ነው፡፡ ማር 5፡37 ኢየሱስ ከጴጥሮስና ከዘቤዴዎስ ልጆች በቀር ማንንም ወደ ምኩራብ አለቃ ቤት እንዲገቡ እንዳልፈቀደ እናያለን፡፡

እንዳውም በደቀመዛሙርቱ መካከል እንኳ ጴጥሮስ ነው መሠረት ሆኖ የሚቆመው፡፡ እርሱ ብቻ ነው ጌታውን በውኃ ላይ በመሄድ የበለጠ ለመቅረብ የሞከረው፡፡ እርሱ ብቻ ነው 12ቱን ወክሎ የሚናገረው፡፡ ኢየሱስ ለሁሉም ደቀመዛሙርት ጥያቄ ሲያቀርብ ጴጥሮስ ነው ሚላሽን የሚሰጠው (ማር 8፣29) ከመገለጥ ተራራ ጴጥሮስ ነው ድንኳኖችን የመሥራት ሀሳብ ያቀረበው (ማር 9፡5)፡፡ ደቀመዛሙርት ሁሉ መልስ የሚያስፈልጋቸውን ጥያቄዎች የሚጠይቀው ጴጥሮስ ነው (ማቴ 18፡21)፡፡ በሉቃ 22፡8 ጴጥሮስና ዮሐንስ ናቸው ፋሲካን እንዲያዘጋጁ የተነገራቸው፡፡ የደቀመዛሙርት ዝርዝር በተፃፈበት ሁሉ ጴጥሮስ የመጀመሪያ ሥፍራ ላይ ነው፡፡ በማቴ 10፡2 ላይ ያለው ዝርዝር በርግጥ ‹‹የመጀመሪያው›› ብሎ ይጠራዋል (በግሪክ ኘሮቶስ)፡፡ ከትንሣኤ በኋላ መልአኩ ‹‹ሄዳችሁ (ለኢየሱስ) ለደቀመዛሙርቱና ለጴጥሮስ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል›› (ማር 16፡7) አለ፡፡ የኢየሩሳሌም ባለሥልጣናት በሐዋሪያት ለይ ተቃውሞ ሲያነሱ ጴጥሮስ ነው ስለ ወንጌል የተከራከረው (ሐዋ 4፡8 5፡29)፡፡ በተለይም በማርቆስ ወንጌል የጴጥሮስ ሥፍራ ቅርበት ጐልቶ ይታያል፡፡ ባህሉን ከመጠበቅ አንፃር ማርቆስ በሮም የጴጥሮስ ትምህርት ድምጽ ማስተላለፊያ ጽሑፍ ነው (Why Four Gospels የሚለውን መጽሐፌን ተመልከቱ)

ማንም ሰው ጴጥሮስ በኢየሱስ ሐዋሪያነት መካከል የተጫወተውን ሚና አይዘነጋም፡፡ ጴጥሮስ በ1 ጴጥ 5፡1 ስለራሱ ሲናገር ‹‹ዋና መጋቢ›› ወይም ‹‹የበላይ›› ሽማግሌ አላለም፣ ነገር ግን ‹‹ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ›› (ግሪኩ ሱምኘረስ ቡቴሮስ)? ወይም አብረው ያሉ ሽማግሌዎች የተሰጣቸውን ማኅበር በኃይል እንዳይገዙ ይነግራቸዋል (5፡3)? ወይም ኢየሱስን ‹‹የእረኞች አለቃ›› (ዋና መጋቢ) ብሎ ይጠራል (5፡4)?

ይህ በፍፁም ልያስደንቀን አይገባም፡፡ በአዲስ ኪዳን ከክህነት የተገለሉትን የሚያመለክት ሀሣብ ፈጽሞ የለም፡፡ በጥንቱ ክርስቲያን መካከል የተቀደሰ ሰው የለም፣ ራስ የለም፣ የበላይ መሣሪያ የለም፣ ቡድንን የሚመራ ‹‹ካህን›› የለም፡፡ የክህነት የበላይነት የመጣው ብዙ ቆይቶና ከአዲስ ኪዳን አንድ ትውልድ አልፎ ነው፡፡ ጀምስ ዱን (James Dunn) በአለም አንዱ ተዋቂ የአዲስ ኪዳን ምሁር እንደጠቆመው አያደገ የመጣው ተቋማዊነት የቀድሞው ካቶሊካዊነት ግለጽ ምልክት ነው፡፡ ቤ/ክ ከተቋም ጋር የበለጠ እየተዛመደች ስትሄድ፣ ሥልጣንን ከቢሮ ጋር ማያያዝ እያደገ ሲመጣ፣ በካህናትና በምዕመናን መካከል ያለው ልዩነት በራሱ እያደገ ሲመጣ፣ የፀጋ ትርጉም ወደ ቅዱስ ምንም እንኳን በሁለተኛው ትውልድ ስዕሎቹ መቀየር ቢጀምሩና (“unity and diversity in the New testament," P.351). ሥርዓቶች እያደለ ሲመጣ ነው፡፡እነዚህ ሁሉ ነገሮች በመጀመሪያው ትውልድ ክርስቲና የሌሉ እንደሆነ ከላይ አይተናል

በክርስቶስ ካለ ግልጽነት ምን ያህል ርቀናል፡ ሐዋሪያት የመሪነትን ትርጉም ከመንገር አንፃር በጣም ግልጽ ናቸው፡፡ በጴጥሮስ ንግግር ውስጥ ያለው በሌሎች ላይ የበላይ እንደሆንን መንጋውን ‹‹በኃይል መግዛት›› አልነበረም፡፡ የመሪነት አገልግሎት የበታችነት አገለግሎት ነው (1 ጴጥ 5፡3)፡፡ አንድ ቀን የዚህ ጉዳይ እውነታ ለእግዚአብሔር ህዝብ የሚያከራክር ወይም ግራ የሚያጋባ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ባህላዊ የሆነው አንድ ‹‹መጋቢ›› በአጥቢያ ቤ/ክ የሚለው ሀሣብ ለመጽሐፍ ቅዱስ ባዕድ የሆነ ነው፡፡ የሚቆጣጠሩ ሽማግሌዎች በበጐቹ ባለቤት የተሾሙት በትህትና እንዲተገብሩና በእነርሱ መካከል ‹‹በእነርሱ ላይ ሳይሆን›› ገዥ መሪ እንዳይሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ የበላይ በሆነ መሣሪያ ያልተገለገለች ቤ/ክ እውነተኛዋ የአዲስ ኪዳን ቤ/ክ ትባላለች፡፡

በአዲስ ኪዳን ብቸኛው ‹‹የበላይ መሣሪያ›› ዲዮትራፌስ ‹‹የመጀመሪያ ሊሆን የሚወድና›› አለቃ ለመሆን የሚፈልግ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት መሪ በሐዋሪያው ዮሐንስ ተወግዟል (3ኛ ዮሐ 9-10)፡፡

የአጥቢያ ቤ/ክችንን ልምምዶች ከእግዚአብሔር ቃል በታች የሚናደርግበት ጊዜ ደርሷል፡፡ በባህላችን ከአዲስ ኪዳን መገለጥ ጋር የሚቃረን ልምምዶች ካሉ ያለን አንድ ምርጫ ብቻ ነው ይኸውም ልምዶቻችንን ማረም ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የካህነትና የምመናን ክፍፍሎችን ይቃወማል፡፡ ሁሉም የአጥቢያ ቤ/ክ አባላት በተሰጣቸው ፀጋ በአከሉ ውስጥ መስራት አለባቸው (ሮሜ 12፡1-8)፡፡ ቤ/ክ እያንዳንዱ ክርስቲያን ‹‹ካህን›› ሆኖ ለእግዚአብሔር መንፈሳዊ ‹‹መስዋዕት›› የሚያቀርብበት መቅደስ ነዉ፡፡ (1ጴጥ 2፡5-9)፡፡ እንደ አዲስ ኪዳን ሁሉም ክርስቲያን መንፈሳዊ ሥጦታውን በመለማመድ የአገልግሎት ሥራውን መፈፀም አለበት፡፡ ማናቸውም በመሪና በተመሪ መካከል ያለ ተገቢ ልዩነት (1ኛ ተሰሎ 5፡13-17) ሁሉም አማኞች ካህን የሚሆናቸውን መሰረታዊ እውነት መጣረስ አይችልም፡፡

ፊል ላንካስተር ትክክል ነው፡- ኢየሱስ እራሱ የበላይነት ሥፍራን መፈለግን እየተቃወመ እያለ (ማቴ 23፡8) መጋቢ ዋናና የተለየ ሥፍራ መፈለግ ለክርስቶስ ኢየሱስ ስድብና ለሌለው ሰው ዘለፈ ነው፡፡ የቤ/ክ ዋና መጋቢ ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ ሌሎቻችን ወንድሞች ነን፡፡ R.T. France በማቴዎስ ወንጌል በተንደል ኮሜንተሪ (ማብራሪያው) የሚያስታውሰን ‹‹[ኢየሱስ] ብቻ ነው ‹የሙሴ ወንበር› የሚገባው፡፡ ደቀ መዛሙርት አንዳቸው ለሌላቸው የሚሰጡትን ይህንን ልዩ የኢየሱስ ሥልጣን የሚፃረር ማንኛውንም የክብር ማዕረግ መጠሪያ ማስወገድ አለባቸው፡፡ የዛሬዋ ቤ/ክ በትኩረት መቀበል ያለባት ምክር በቤ/ክ የሚሰጠው የቅስና ማዕረጐች በተገናኘ ብቻ ሳይሆን (‹‹በጣም የተከበሩ›› ‹‹ጌታዬ›› ‹‹ጳጳስ›› በተለይም በትምህርት ደረጃ የሚመጣውን የበዛ ልዩነት ወይም በቤ/ክ ያለ የሥልጣን የበላይነትም ነው፡፡

ይህንን ተረድታችኋል? ይህ ከሆነ አሁን የክርስቲያን ወንጌል ዋና ነገሩን እያያችሁ ነው ማለት ነው፡፡ የማንኛውም መጽሐፍ መልዕክቱ በእግዚአብሔር ፊት የሰው መሰረታዊ ችግር ትዕቢቱ እንደሆነ ከማወጅ አላለፈም፡፡ አብዛኛው ሰው ሰራሽ የሆነ የቤ/ክ አሰራሮቻችን በእርግጥ ለነቀፋ የተገለጡ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ይህንን ያህል ደረጃ ወደታች መቼም የደረሱ አልነበሩም፡፡ እውነተኛ የክርስቲያን ደቀመዛሙርትነት ሁል ጊዜ የባህል ተቃራኒ ነው፡፡ የዚህ ግልጽ ምልክት ኢየሱስ የመጀመሪያ ሊሆን የሚወድ የሁሉ በሪያ ይሁን ያለው ነው (ማር 10፡44)፡፡ ይህም ታላቅነት የሚመጣው በአገልግሎት ሲሆን፣ ህይወታችንን በመስጠት ህይወትን የሚንገኝበት ብቸኛ መንገድ ነው፡፡

እነዚህን ነገሮች በማጠቃለያ በአራት መንገዶች ላሳያችሁ፡- የቤ/ክ መሪ ከሆንክ በመጀመሪያ ደረጃ እነዚያን በብሮህ ግድግዳ ያሉ ተራ ዲኘሎማዎችን ታወርዳቸዋለህ? በምዕመናንህ መካከል እንደውም ህሊናው የሳተ እንኳ በዚህ አይማረክም (እንዲህ ልበል አንተ እራስህም መሆን የለብህም)፡፡ ሁለተኛው ማወቅ የለብህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሽምግልና ለኃይማኖታዊ ማዕረጐች ምንም ቦታ የለውም ወይም ትልቅ ሥፍራ ለሚሰጣቸው እንደ ‹‹ዋና መጋቢ›› ‹‹ረዳት መጋቢ›› ‹‹የተከበሩ›› ለመሳሰሉት ማዕረግ ከፈለጋችሁ ‹‹ሽማግሌ›› ‹‹ወንድም›› የሚለው በቂ ነው፡፡ ሦስተኛ ‹‹የአንድ ሰው መጋቢ›› ሐሣብ ከያዛችሁ ከዚያ ውጡ፡፡ በአዲስ ኪዳን የምንማረው ኃላፊነትን የመከፋፈል መሪነት ብቻ ነው፡፡ በጋራ የሚደረግ መሪነት ብቻ ክርስቶስ ብቻ የቤ/ክ ራስ እንደሆነ የሚገልጠውን የአዲስ ኪዳን ክህነት ያበረታታል (ቆላ 1፡18)፡፡ በመጨረሻም እራስህን በምታደርገው ሁሉ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ለመሄድ አስገዛ፡፡ ማንኛውም በክርስቲያን ሕይወት የሚሆነው ነገር በእግዚአብሔር ቃል የተገነባ መሆን አለበት፡፡

የእረኞች አለቃ የክብር በላይነት ማንም ልወዳደረውና ልቀርበው በማይችል ክብርና እርገት የታየበትን ይህም ለአገልግሎቱ መሠረት የሆነውን አይተሃል? የራስህን ድካምና ኃጢአት አስብ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው እኔም ጨምሬ ሊባልና አንተም አድርግ፡፡ በሰማይ እነዚህ ነገሮች በተሻለ ሁኔታ መረደት በሚቻልበት ቦታ ሰዎችና መልአክት የነገሥታትን ንጉሥና የጌቶችን ጌታ ለማመስገን በአንድነት ይሆናሉ (ራዕ 19፡16)፡፡ እዚህ በምድር በፀጋው የማይገባ እረኛነት ሥር የሆኑትና ይህንንም የተቀበሉ አንደዚያው ይሆናሉ፡፡

June 12, 2010

David Alan Black is the editor of www.daveblackonline.com.

Back to daveblackonline