restoring our biblical and constitutional foundations

                

አናባፕቲስቶችን ለምን ወደድኳቸዉ

 David Alan Black  

የ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አናባኘቲስቶች ክርስቶስን ስለመከተል ብዙ የሚያስተምሩን ነገር አለ፡፡ ደቀመዛሙርትነት-የክርስቶስን ምሳሌነት መከተል ዋናው አናባኘቲስቶች የእምነት ህይወትን የሚገልጠበት መመዘኛ ነው፡፡

አናባኘቲስቶች የቆሙላቸው ነገሮች ከዚህ ቀጥሎ ያሉ ናቸው፡፡

የሚያምኑት፡-

-   በመግዛት ፈንታ ማገልገል

-   በመለያየት ፈንታ የልዩነትን ግድግዳ ማፍረስ፣

-   በቤ/ክ የሥርዓት ባህል (ትውፊት) ፈንታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጣን፣

-   በሥልጣን ተዋረድ የበላይና የበታች መሆን ፈንታ ወንድማማችነት

-   በሳይፍ ፈንታ ፎጣ

-   በመጋቢ ፈንታ የክርስቶስን ራስነት

-   በጦርነት ፈንታ የሠላም መንገድ

-   ቤ/ክንን እንደ ድርጅት በማየት ፈንታ እንደ ሕያው አካል መቀበል

-   በፖለቲካ መንግሥት ፈንታ የእግዚአብሔር አገዛዝ

-   በሃይማኖተኛነት ፈንታ የውነተኛዋ ዓለም አቀፋዊነት ቤ/ክ

-   ከሥርዓት ኃይል ይልቅ የመከራ ኃይል

-   መጽሐፍ ቅዱስን የሥነ መለኮት ምሁራን መጽሐፍ በማድረግ ፈንታ የቤ/ክ መጽሐፍ አድርጐ መቀበል

-   ለአለቆችና ኃይላት ታማኝ ከመሆን ይለቅ ለሰማያዊ ዜግነታቸው ታማኝ መሆን

-   በመዋቅሮች ግፍት ካለ የቤ/ክ ህይወት ይልቅ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ያተኮረ ሕይወት

-   በክርስቲያን ብቻ ተወስኖ ከመቅረብ ይልቅ ለህዝቦች ብርሃን መሆን

-   መከራን በማምጣ ፈንታ መከራ መቀበል

-   ስለ ክርስቶስ ከማወቅ ብቻ ይልቅ ክርስቶስን ማወቅ

-   ሙት በሆነ ቀጥተኛ /እውነተኛ ትምህርት ፈንታ የሚሰራ እምነት (በሁለቱም አቅጣጫ)

-   ፀጋን እንደ ሥነ-መለኮት ቀኖና ፈንታ እንደ ሕያው እውነታ፣

-   ከተሾሙት አገልግሎት ብቻ ይልቅ የእያንዳንዱ አባል አገለግሎት

-   በመጠመቅ ፈንታ በክርስቶስ መጠመቅ

-   በስም ብቻ ከገነነ አንድነት ይልቅ በኑሮ የሚገለጥ አንድነት፣

-   የተገለሉትንና የተጣሉትን ችላ በማለት ፈንታ መቀበል፣

-   በሥነ አፈታት እውቀት ፈንታ የሥነ አፈታት መታዘዝ፣

June 12, 2010

David Alan Black is the editor of www.daveblackonline.com.

Back to daveblackonline