restoring our biblical and constitutional foundations

                

የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቤ/ክ

 David Alan Black  

  ሥልጣን አሜሪካንን ጐድቷታል በግ ክንፍ (liberals) ብቻ አይደለም አሁንም በቀኝ ክንፍ (conservatives) ተመሳሳይ ነገር እያደረገ ነው፡፡ ይህንን ችግር (Why I Stopped Listening to Rush: Confessions of a Recovering Neocon) በሚለው መጽሐፌ ተንትኛለሁ፡፡ ቀኝ ክንፍ ብዙ ተከታይ አለው:: ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ስዞርም ሁሉንም ተከታዮች ወደ ስህተት ይመራል፡፡ በታወቀ ቦታ ሁሉና መፈክር ባለበት ሥፍራ ሁሉ ተቀባይነት አለው፡፡ እራሱን በኃይል፣ በማዕረግና በሐብት ሸጧል፡፡ ጥቂቶች ብቻ ናቸው ይህ ዝንባሌ ቤ/ክንን ማጥቃቱን የሚክዱት፡፡ በጨለማ ውስጥ አንድ ትንሽ ብርሃን ብቻ ነው የቀረው ይኸውም ንጹህ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ አንድን መሰረታዊ እውነታዎችን መመለስ አሁንም ይቻላል፣ ግን ይህም የሚሆነው የእግዚአብሔርን ቃል ስንታዘዝ ብቻ ነው፡፡ እዚህ  ጋር ነው የአለቃው የአእምሮ ብርሃን ሙሉ በሙሉ የተገለጠው፡፡ የሥልጣን ዘውድን ወደ ራሱ ላይ አወጣ፡፡

  አሁን ያላቸውን ቤ/ክ ህይወት ልምምድ መንገድ ታህድሶን የሚጀምርበት ቦታ እንደመሆኑ በትኩረት ማየት አለብን፡፡ ተክትኮችን በመለጋትና በማስካድ ፈንታ የተለየ ዘዴ ማዘጋጀትና መስማማት አለብን፡፡ እውነቱን ለመናገር ወደ ፊትም የዛሬዋ ቤ/ክ ህይወት ተለምዶዎች በተዋሰነ ደረጃ የሚቀጥሉ አሉ፡፡ ይሁን እንጅ መመለስ የማይፈልጉና በሚገባ የሚመረምሩ ላይሆኖ ይችላሉ፡፡ የተቀነባበሩ ሀሳቦች (አሁን እየተገለጡ ያሉ ቤ/ክርስቲያናት አስተሳሰቦችን ጭምር) ልሰሩ እንደማይችሉ አኔ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ተመሳሳይ ገንዘብ የሚከፈለው ሰራተኛ፣ ሕንፃ፣ የንግድ ሥራ፣ ፀሐፊዎችና ብዙ ትልቅ ቤ/ክ አንደሚያደርጉት ተቋማዊነት አላቸው፡፡ ዋናውን ነገር ቤ/ክ እንደመጽሐፍ ቅዱስ ማየት ወደ መጨረሻ መዳረሻ መንገድ ማየታችን ነው፡፡ ይህም እግዚአብሔር አዲስ ሰው የሚቀርጽበት መንገድ መንፈሳዊ መንግሥት ከሰው ሥንፍና የምወጣበት ነው፡፡ ጊዜው አስተማሪ የሆኑ አዲስ ሀሳቦችን የምናቅድበት ነው፡፡ ብዙ የቤተክርስቲያን ሰዎች ምን ሊደረግ እንደሚችል እየጠየቁ ነው መንፈስ ቅዱስ ከፈቀደና አብሮን ከሠራ ለውጥ ይመጣል፡፡ ለውጡም ለተሻለ ነገር፣ ለመንግሥቱ መስፋትና ለአግዚአብሔር ክብር ነው፡፡

የታደሰችው የ21ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ቤ/ክን ምን ትመስላለች? የምታገለግል ቤ/ክ ትሆናለች፣ የድርጅቱ መዋቅር ግልጽና ቀለል ያለ ውጣ ውረድ ለሚያስዙ (በቢሮክራቶች)ና ውጣ ወርድ በበዛበት አሰራር (ቢሮክራሲ) የተጨናነቀ አይሆንም፡፡ የገንዘብ አጠቃቀሙ ቅድሚያ የሚሰጠው ለአካባቢና ለአለም አቀፋዊ ሚሽን ነው፡፡

ትላልቅ ወጭዎች ይቀንሳሉ፡፡ ቁጠባዎችም ለደቀመዛሙርት አገለግሎት ይውላሉ፡፡  በአሁን ጊዜ በሚከፈላቸው ሰዎች የሚሰሩ ሥራዎች በፈቃደኛ ሰዎች ይሞላሉ ወይም ይተካሉ፡፡ ቤተእምነቶች በገንዘብ አጠቃቀም ቤ/ክ ገንዘብን በሕትመት ስራ ከማጥፋት (አጫጭር ጽሑፎች፣ በየጊዜ የምዘጋጅ የሰንብት ትምህርቶች (መጽሐፍ ቅዱስ በፈንታው ይሰራል)ና የተዋቡ መጽሄቶች) ለውጥ ያደርጋሉ፡፡ የቤ/ክ ሕንጻዎች ለመጀመሪያውና ሁለተኛ ደረጃ የክርስትና ትምህርት ይሆናሉ፡፡ አማኞች በደስታ ከቤተእምነት አልፎው በፈቃደኝነት ይሰራሉ፡፡ በተለይ በአጥቢያ ደረጃ ቤ/ክ የወንጌልን መልካም ዜና ቅደምያ ሰጥታ ተዉጃለች፡፡ በዚህም ባህል የሚጠይቃቸውን ነገሮች ወደ ጐን ሳንተው ሙሉ ፈቃደኝነት ያለበት የምእመናን አገልግሎት የቀሳውስትን ስራ ይተካል፡፡ አማኞች በግላቸው አንደስጦታቸው ያገለግላሉ፡፡ ቤ/ክ ለምዕማናን ሁሉ የሚሆን ሥልጠና (ሴምናሬዎች እየረዱቸው) ያዘጋጃሉ፡፡ እንዲሁም በፈቃደኞች ላይ የተመሰረተ የትምህርት ኘሮግራሞችን በመዋቅራቸው ውስጥ ያካትታሉ፡፡ አምልኮ በተወሰነ ቦታና ጊዜ አይገድብም፡፡

በአቢያተ ቤ/ክናት ግንባታ እንደ ጣዖት ልታይ ይችላል፡፡ ቤ/ክ ለርሷ ጥቅም መታገል የለባትም ግን አገልጋይ መሆን አለበት፡፡ አለማዊነትን በመግለጥ እንብ ማለት አለባት፡፡ የሰናጠሉ መጋቢዎች ለእያንዳንዱ ‹‹አገልጋዮች›› ለምዕመናን ረዳት ይሆናሉ፡፡ እንደዚህ ባተደሳች ቤ/ክ በተሰበሰቡ ጊዜ ሁሉ ወደ ፊት የሚጓዙ ደቀመዛሙርትን እናገኛለን፡፡ አዲስ አባል በህብረተሰብ መካከል ያሉትን ተግባሮችን ለይቶ እንድሳተፍ ይጠየቃል፡፡ (ጉረቤትን መምከር፣ ፈቃደኛ የሆነ የቤተመጽሐፍት አባል፣ ቤት ለቤት መጐብኘት ወዘተ) ይህም በቤተክርስቲያን ካለው አገልግሎት በተጨማሪ ነው፡፡

እነዚህ ያነሣኋቸው ነጥቦች (በተጨማሪ የተደሳች ቤ/ክ መልካም ምሳሌዎችን ማቅረብ እችላለው) የእኔን ሀሣብ ብቻ የሚያመላክቱ አይደለም፡፡ በጣም ብዙ በሆኑ ጥናቶች የተደገፈና በተለማመድናቸው በትልልቅ መዋቅሮች ተቃርኖ የሚታዩ ናቸው፡፡ የክርስትናን ሥርዓት ትዕይትን ካመጣው የተያያዘ ነው፡፡ የእምነት ጦርነት በክርስትና ላይ የተከፈተ ጦርነት አይደለም፡፡ ክርስትናን ከማይነቃነቀው ሥርዓት ነፃ በማውጣት ጣዖቶቻቸውን ለማፍረስና በመንፈስ ድህነት የምትታወቀውን ቤ/ክ በድጋሚ ለመመስረት ነው፡፡

June 12, 2010

David Alan Black is the editor of www.daveblackonline.com.

Back to daveblackonline